Home Sport News ሄንሪ ራሱን ከማህበራዊ ሚዲያ አገለለ

ሄንሪ ራሱን ከማህበራዊ ሚዲያ አገለለ

by sam

የቀድሞው የአርሰልና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ቲዬሪ ኦንሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ የዘረኝነትና ሌሎች መሰል የበይነ መረብ ጥቃቶችን በመቃወም ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዳገለለ አስታውቋል።

የ43 ዓመቱ ኦንሪ 2.3 ሚሊዮን ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ አርብ ዕለት ባስተላለፈው መልዕክት ችግሩ በጣም አሳሳቢ እንደሆነና ችላ ለማለት እንኳን ከባድ እንደሆነ ገልጿል።

ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመለሰው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ኮፒራይት (የባለቤትነት መብት) ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ እንደሆነ ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ የተሻለ እርምጃ መወሰድ እንዲጀመር መጠየቁን ቢቢሲ/BBC ዘግቧል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish