Home Sport News ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሀገር አቀፍ የክብር የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበረከተ

ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሀገር አቀፍ የክብር የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበረከተ

by sam

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በኦሊምፒክ እና በሌሎች ውድድር መድረኮች ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ላደረገችው ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሀገር አቀፍ የክብር የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶላታል። 

350 ግራም የሚመዝነውን የወርቅ ኒሻን ሽልማቱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አበርክተውላታል። 

ከኒሻኑ በተጨማሪም 2021 ሞዴል የሆነች ሌክሰስ ቪ8 መኪና በአገር አቀፍ ደረጃ ተበርክቶላታል። 

ለደራርቱ ቱሉ አገር አቀፍ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከክብር ሽልማቱ እና ከመኪናው በተጨማሪ የተለያዩ ሽልማቶችም ተበርክተውላታል። 

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish