Home Sport News ፈረንሳይ ነጥብ ጥላለች

ፈረንሳይ ነጥብ ጥላለች

by sam

ወሳኝ ቁልፍ ተጫዋቿን ዶሚኒክ ስቦዝላይን በጉዳት ያጣችው ሀንጋሪ በደጋፊዎቿ ፊት ከ አለም ዋንጫ አሸናፊዋ ፈረንሳይ ጋር ነጥብ ተጋርታ መውጣት ችላለች ።

• ሀንጋሪን መሪ ያደረገች ግብ ያስቆጠረው አቲላ ፊዮላ ሁለተኛ ጎሉ ሆኖ ተመዝግቧል ።

• ከ 500 ደቂቃዎች በላይ ግብ ያላስተናገዱት ፈረንሳዮች በ ፊዮላ አማካኝነት ግብ ሊቆጠርባቸው ችሏል ።

• አንቱዋን ግሪዝማን በአውሮፓ ዋንጫው ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ከ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሚሼል ፕላቲኒ በመቀጠል ሶስተኛው ከፍተኛ አግቢ ሆኗል ።

• ፖርቹጋል ከደቂቃዎች በኋላ ጀርመንን የምታሸንፍ ከሆነ በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ታረጋግጣለች ።

• በቀጣይ የምድቡ ጨዋታዎች ፈረንሳይ ከ ፖርቹጋል እንዲሁም ሀንጋሪ ከ ጀርመን የሚጫወቱ ይሆናል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish