Home Sport News ዮሚፍ ቀጀልቻ ድርብርብ ድል አስመዝግቧል

ዮሚፍ ቀጀልቻ ድርብርብ ድል አስመዝግቧል

by sam

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በ ኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ከ ደቂቃዎች በፊት በተደረገ የ 3,000 ሜትር ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸንፏል ።

ዮሚፍ 7:26.25 በሆነ ደቂቃ በመግባት የግሉን ምርጥ ሰዓት እንዲሁም የ ቦታውን ሪከርድ በመስበር ውድድሩን በ በላይነት ማጠናቀቅ ችሏል ።

ዮሚፍ በ ጀግናው አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ተይዞ የቆየውን የ ቦታውን ሪከርድ 1.17 ሴኮንዶቻ በማሻሻል ሪከርዱን ሰብሯል ።

ዮሚፍ ቀጀልቻ በ ኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የገባበት ደቂቃ የአለማችን ሰባተኛው ፈጣን ሰዓት መሆኑ ይፋ ተደርጓል ።

ከዚህ በተጨማሪም የ ዮሚፍ ቀጀልቻ ድል የ ዳይመንድ ሊግ አዲስ ሪከርድ በመሆን ተመዝግቧል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish