Home Sport News የቀድሞው የአርሰናል አምበል ፓትሪክ ቪዬራ የፓላስ አሠልጣኝ ሆኖ ተሾመ

የቀድሞው የአርሰናል አምበል ፓትሪክ ቪዬራ የፓላስ አሠልጣኝ ሆኖ ተሾመ

by sam

የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተወዳዳሪዎቹ ክሪስታል ፓላስ የቀድመው የአርሰናል አምበል የሆነው ፓትሪክ ቪዬራን አሠልጣኝ አድርገው መቅጠራቸውን ይፋ አደረጉ።

ቪዬራ፤ ሮይ ሆጅሰንን ተክቶ ነው የፓላስ አሠልጣኝ ሆኖ የተሾመው።

የቀድሞው የአርሰናል አምበል የነበረው ፓትሪክ ቪዬራ ከረዥም ጊዜ ውይይት በኋላ ነው የፓላስ አሠልጣኝ ለመሆን የተስማማው።

ሮይ ሆጅሰን ፓላስን ለመልቀቅ እንደወሰኑ ያሳወቁት ባለፈው ግንቦት ነበር።

የ45 ዓመቱ ፈረንሳዊ ባለፈው የውድድር ዘመን 14ኛ ሆነው ካጠናቀቁት ፓላሶች ጋር ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish