Home Sport News እንግሊዝ ለ አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜው አልፋለች

እንግሊዝ ለ አውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜው አልፋለች

by sam

አስቀድመው በ ዳምስጋርድ ጎል መምራት የቻሉት ዴንማርኮች ሲሞን ካየር በራሱ ላይ እንዲሁም ኬን ባስቆጠረው ግብ ሽንፈት አስተናግደዋል ።

• ሀሪ ኬን በ ካስፐር ሽማይክል ላይ አስራ አምስተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ።

• ሀሪ ኬን በ አውሮፓ ዋንጫው ያስቆጠራቸውን የ ግብ መጠን ወደ አራት ከፍ አድርጓል ።

• በአውሮፓ ዋንጫው በራስ ላይ የተቆጠሩ የግብ መጠን ወደ አስራ አንድ ከፍ ብለዋል ።

• እንግሊዝ በ ዘንድሮው የ አውሮፓ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብ ተቆጥሮባቸዋል ።

• ጆርዳን ፒክፎርድ ከ 480 ደቂቃዎች በኋላ ግብ ሊቆጠርበት ችሏል ።

• እንግሊዝ በ አለም አቀፍ ውድድሮች ለ ፍፃሜ ስትደርስ ከ ሀምሳ አምስት ዓመታት በኋላ ነው ።

• እንግሊዝ በ ፍፃሜው በ ዌምብሌይ ስታዲየም የፊታችን እሁድ ምሽት ጨዋታቸውን ከ ጣልያን ጋር የሚያካሂዱ ይሆናል ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish