Home Sport News አራት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ሲሞን ከቶኪዮ የፍፃሜ ውድድር ራሷን አገለለች

አራት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዋ ሲሞን ከቶኪዮ የፍፃሜ ውድድር ራሷን አገለለች

by sam

አሜሪካዊቷ የጂምናስቲክ አትሌትና አራት ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ሲሞን ባይልስ በቶኪዮ በነገው ዕለት ከሚደረገው የጂምናስቲክ የፍፃሜ ውድድር ራሷን ማግለሏን አስታውቃለች።

በአለም በጂምናስቲክ ስፖርት ዘርፍ የምንጊዜውም ምርጥ የሚል ስም ማትረፍን የቻለችው አትሌቷ ከሴቶች ቡድን የፍፃሜ ውድድር ራሷን ያገለለችው በአዕምሮ ጤንነቷ ላይ ማተኮር ስላለባት መሆኑንም ተናግራለች።

የአሜሪካ ኦሊምፒክ ቡድን መሪ እና አትሌቶችም ሲሞን ለአእምሮ ጤንነቷ ቅድሚያ ለመስጠት መወሰናቸውን አድንቀዋል።

የ 24 ዓመቷ አትሌት በቶኪዮ አምስቱን የግለሰብ የጂምናስቲክ ዘርፍ ፍፃሜዎች ደርሳለች።

በመጪው ሃሙስ ‘ኦል አራውንድ’ በተባለው ውድድር የቀደመ አሸናፊነቷን ለማስጠበቅ መሳተፍ ነበረባት። ከዚያ በኋላም በመጪው እሁድ፣ ሰኞና ማክሰኞም ሌሎች በጂምናስቲኩ ዘርፍ ባሉ ውድድሮችም መሳተፍ አለባት።

የአሜሪካ ጂምናስቲክስ እንዳለው “ሲሞን በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄዱት የግለሰብ የፍፃሜ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ወይም ላለመሳተፍ መቻሏንም በተመለከተ በየቀኑ ትገመገማለች” ብሏል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish