Home Sport News አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ5 ኪ. ሜ የሩጫ ውድድር የአለም ሪከርድ ሰበረች

አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ5 ኪ. ሜ የሩጫ ውድድር የአለም ሪከርድ ሰበረች

by sam

በሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ  አትሌት ሰንበሬ  ተፈሪ የአለም ሪከርድ ሰብራለች፡፡

አትሌቷ  በሄርዞጌናውራች በተካሄደው የ‘አዲዜሮ ሮድ ቱ ሪከርድስ’ ውድድር ነው 14 ደቂቃ ከ 21 ሰከንድ በመግባት  ሪከርዱን የሰበረችው፡፡

አትሌቷ ያሻሻለችው ሪከርድ ሴቶች ብቻ በሚወዳደሩበት ሩጫ በአትሌት ቤትሪስ ቼፕኮች የተያዘውን 14 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ  እና በወንዶች እና ሴቶች ድብልቅ ውድድር በአትሌት ሲፈን ሐሰን የተመዘገበውን 14 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ  ብቻ ሳይሆን በሪከርድነት ገና ለመመዝገብ ሂደት ላይ ያለውን 14 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ የሆነ የአትሌት ጆይሲሊን ጄፕኮስጌ ፈጣኑን ሰዓት ጭምር መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።

በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር  ደግሞ አትሌት ታደሰ ወርቁ 26 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን  በ2ኛነት አጠናቋል።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish