Home Sport News ኢትዮጵያውያኑ ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በበርሊን ማራቶን አሸናፊ ሆኑ

ኢትዮጵያውያኑ ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በበርሊን ማራቶን አሸናፊ ሆኑ

by sam

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጎተይቶም ገብረ ስላሴና ጉዬ አዶላ በጀርመኗ መዲና በርሊን በተካሄደውን የማራቶን ውድድር በሴቶችና በወንዶች ዘርፍ በአንደኛነት አጠናቀዋል።

በሴቶች የማራቶን ውድድር ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ስፍራ የያዙት ኢትዮጵያውያን ናቸው።

በወንዶች የማራቶን ውድድር ከፍተኛ ግምት የተሰጠውና ከወራት በፊት ከኮሮናቫይረስ ህመም ያገገመው ቀነኒሳ በቀለ በሶስተኛነት አጠናቋል።

ጉዬ አዶላ በ2፡05፡45 ሰዓት የአሸናፊነቱን ስፍራ ሲይዝ ኬንያዊው የጎን ቤትዌል ሁለተኛ፣ ቀነኒሳ በቀለ ሶስተኛ፣ ታዱ አባተ አራተኛ ስፍራን ይዟል።

የ30 አመቱ ጉዬ አዶላ ከዚህ ቀደም በበርሊን ማራቶን የመጀመሪያ በሆነው ውድድር የአለም ክብረ ወስንንና ሁለት ጊዜ የአለም ሻምፒዮና ከሆነው ኢሉይድ ኪፕቾጌን በመከተል ሁለተኛ ወጥቷል።

በሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ጎተይቶም ገብረሥላሴ የበርሊን የማራቶን ውድድር የመጀመሪያዋ ነው።

ጎተይቶም ይህንን ውድድር በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ09 ስታጠናቀቅ ሕይወት ገብረ ኪዳን በ2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ሁለተኛ በማሸነፍ የብር ሜዳሊያዋን አሸንፋለች። በሶስተኛ ደረጃም ኢትዮጵያዊቷ ቶላ በሶስተኛነት ውድድሩን አጠናቃለች።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish