Home Sport News አጫጭር መረጃዎች እና ውጤቶች

አጫጭር መረጃዎች እና ውጤቶች

by sam

• ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ ለ ባየር ሙኒክ 100ኛ ጨዋታውን አድርጓል ።

• በሴርያው ደካማ ጉዞ ላይ የሚገኙት ጁቬንቱሶች በ ሻምፒየንስ ሊጉ ከወዲሁ አስራ ስድስት ውስጥ መግባታቸውን አረጋግጠዋል ።

• ሊዋንዶውስኪ ሀያ ስምንተኛ ሀትሪኩን በእግር ኳስ ህይወቱ መስራት ችሏል ።

• ሮናልዶ በአራት ተከታታይ የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር የቻለ ቀዳሚው የ ዩናይትድ ተጫዋች ነው ።

• ሊዋንዶውስኪ በ ዘንድሮው የውድድር ዓመት በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ በ አራት ጨዋታዎች ስምንት ጎሎችን አስቆጥሯል ።

• የ አታላንታው የፊት መስመር አጥቂ ዱቫን ዛፓታ በ አስር የሻምፒየንስ ሊግ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ሲያደርግ የ ክለቡ ቀዳሚው ተጫዋች አድርጎታል ።

• ሊሮይ ሳኔ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ስምንት ጎሎችን ሲያስቆጥር ስምንት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ሊዋንዶውስኪ ያስቆጠራቸው ስምንት ጎሎች በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊጉ እየተሳተፉ ከሚገኙ ክለቦች መካከል ከ ሀያ ስድስቱ የበለጠ ነው ።

Leave a Comment

Related Posts

en_USEnglish